የትምህርት ሴክተሩን የሰራተኞች ምዘና ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ
የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በትምህርት ሴክተር ሪፎረም እና የሰራተኞች ምዘና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የትምህርት ሴክተር ሪፎርም፣ ጥናትና ትንተና፤ እንዲሁም የሴክተሩ የሰራተኞች ምዘናን የሚመለከቱ ሰነዶች ቀርበዋል፤ ሰነዶቹን ያቀረቡት ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋረገጥ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ዶክተር አማን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዶክተር ኤፍሬም ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሲሆኑ በርዕሰ ጉዳዮቹ ዙሪያ ከባለስልጣኑ ሰራተኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፤ የትምህርት ሴክተሩን ሰራተኞች ምዘና ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑም ተገልጿል። የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ አብተው በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቂ ማብራሪያ መሰጠቱን ገልጸው የባለሥልጣኑ ሰራተኞች በመድረኩ ያገኙትን ግንዛቤ መነሻ አድርገው በተሰማሩበት የስራ መደብ ሰራተኛ ምዘናውን ለመውሰድ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ በፊስቡክ - https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም - https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www.neta.gov.et ይከታተሉን፡፡