የባለሥልጣኑ አመራሮችና ሠራተኞች የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞች ”ከቃል እስከ ባህል !“በሚል መሪ ሐሳብ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄዱ፡፡ ውይይቱ የብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያስተላለፋቸውና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ብሎ ለይቶ ያስቀመጣቸው ዋና ዋና ነጥቦች ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን የገለፁት በውይይት መድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን ያቀረቡት የተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ የመንግስት ውሳኔ ማንኛውንም የሀገሪቱ ዜጋ የሚመለከት በመሆኑ በጉባኤው የተላለፉ ውሳኔዎች ሁሉም ዜጋ ሊያውቀው የሚገባ በመሆኑ ውይይቱን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ በየደረጃው በትኩረት ይሰራሉ ተብለው በአቅጣጫ ከተመላከቱት መካከል ብቃት ያለው፣ ነፃ፣ ገለልተኛ እና አካታች የሲቪል ሰርቪስ መገንባት፣ ውጤታማ የሠላም ግንባታ ስራዎች፣ የኢኮኖሚ ልመ፣ትን ማሳደግ፣ የፍትሕ ዘርፍ ውጤታማነት ማሳደግ እና የሀገር ግንባታ ላይ መስራት ይጠቀሳሉ፡፡ ማህበራዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ፣ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ፣የአካታች እና አስተሳሳሪ ትርክት ግንባታ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም፣ ጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ላይ በትኩረት እንደሚሠራም ጉባዔው ያስተላለፋቸው ዋና ዋና ውሳኔዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው ፤ የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ፤ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ በፊስቡክ - https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም - https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www.neta.gov.et ይከታተሉን፡፡