ማሳሰቢያ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡-የዲግሪ ህትመትና የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥን ይመለከታል፤
ጉዳዩ፡-የዲግሪ ህትመትና የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥን ይመለከታል፤ በሀገራችን ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሰጡ ዲግሪዎች ህትመት ወጥ በሆነ መልኩ ደህንነታቸው ተጠበቆ የዲግሪ ማስረጃ/ሰርተፍኬት ህትመት በማዕከል ለማሳተም ታስቧል ፡፡ ስለሆነም ከወዲሁ ለምናደርገው ቅደመ ዝግጅት ይረዳን ዘንድ በዲግሪ የምስክር ወረቀቱ ላይ ሊካተትላችሁ የምትፈልጉትን ሎጎና ሌሎች መካተት አለበት የምትሉትን እንድታካትቱ እና በዩኒቨርሲቲያችሁ በዚህ ዓመት የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉና ለምርቃት የተዘጋጁ የተማሪዎች ዝርዝር በመላክ ህትመቱ የሚፈጸም ሲሆን በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሬጅስትራሮች ጋር በሚኖር ሰፊ የውይይት መድረክ ስለ አጠቃላይ አፈጻጸሙ ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች ጀምሮ ከላይ በተገለጸው አግባብ የሚፈጸም መሆኑን በመረዳት የተቀመጠው አቅጣጫ ተፈጻሚ እንዲሆን እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ - https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም - https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www.neta.gov.et ይከታተሉን፡፡