የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች 18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ
“ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት!!” በሚል መሪ ሐሳብ በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በተከበረውን በዓል ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት እና በዓሉን በንግግር የከፈቱት በባለሥልጣኑ የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ እንዳሉት ህዳር 29 ቀን በሀገራችን ታሪክ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ብዝሃነትን ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ያገኝበት እና የተረጋገጠበት እለት መሆኑን ገልጸው ይህን ታላቅ ሀገራዊ በዓል ስናከብር የሚያራርቁን ሳይሆን ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችን አጉልተን በማሳየት አንድነታችን ይበልጥ ማጠናከር አለብን ብለዋል፡፡ የእለቱን የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና የመንግስታት ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ቸሩ በበኩላቸው ስለ ፌዴራሊዝም ጽንሰ ሐሳብ ፤የፌደራል ሥርዓት አስፈላጊነት በኢትዮጵያ ፤ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ያመጣው መልካም አጋጣሚ እና እየገጠሙት ያሉትን ፈተናዎች በመግለጽ የፌደራሊዝም ሥርዓት እንደ ሀገራች ያሉ ብዝሃ ማንነት፣ ሃይማኖት፣ቋንቋ፣ ባህል ፣ ሀብት፣ የቆዳ ሰፋት እና የህዝብ ብዛት ያላቸው አብዛኞቹ ሀገራት የሚከተሉት ስርዓት መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል ፡፡ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እና ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ ለተነሱት አስተያየት እና ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ፡፡